Friday, 17 May 2024 | Login
ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት ስድስት ወራት 8.18 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት ስድስት ወራት 8.18 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

ኢትዮ ቴሌኮም የሦስት ዓመት አዲስ የእድገት ስትራቴጂውን በ2015 በጀት ዓመት መጀመሪያ ካስተዋወቀ በኋላ የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ሪፖርቱን በዛሬው እለት አቅርቧል።የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ እንደተናገሩት ኩባንያው ባለፉት ስድስት ወራት 8.18 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱ ገልፀዋል። ባለፈው ዓመት የኩባንያው የዓመቱ ሙሉ ገቢ 9 ቢሊየን ብር የነበረ ሲሆን በ2015 ዓመት በስድስት ወራት ውስጥ...
 

ኢትዮ ቴሌኮም የሦስት ዓመት አዲስ የእድገት ስትራቴጂውን በ2015 በጀት ዓመት መጀመሪያ ካስተዋወቀ በኋላ የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ሪፖርቱን በዛሬው እለት አቅርቧል።የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ እንደተናገሩት ኩባንያው ባለፉት ስድስት ወራት 8.18 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱ ገልፀዋል።

ባለፈው ዓመት የኩባንያው የዓመቱ ሙሉ ገቢ 9 ቢሊየን ብር የነበረ ሲሆን በ2015 ዓመት በስድስት ወራት ውስጥ የተገኘው ገቢ ካለፈው ሙሉ ዓመት ገቢ ጋር የሚስተካል መሆኑ ተገልጿል።በዘንድሮው ዓመት ለተገኘው ከፍተኛ ትርፍ ዋና ምክንያት የሚሆነው በኩባንያው የተደረገው የወጪ ቅነሳ መርሃ ግብር እና ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ መተግበሩ 3.5 ቢሊዮን ብር ወጪ መቀነስ እንዳስቻለ ፍሬህይወት ታምሩ መናገራቸውን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።

ኢትዮ ቴሌኮም 214 ከሚሆኑ ተቋማት ጋር በቴሌ ብር አጋርነት እየሰሩ ሲሆን ባለፉት ስድስት ወራት 217 ቢሊየን ብር በቴሌ ብር መዘዋወሩ ተጠቁሟል ።ኢትዮ ቴሌኮም አጠቃቀምን ለማሳደግ የሚያስችሉ የኔትወርክ ማስፋፊያ ፣ የአገልግሎት ጥራት ማሻሻያ እንዲሁም የደንበኞችን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ 50 አዳዲስ እና 41 ነባር በድምሩ 91 የሀገር ውስጥ እና የዓለም አቀፍ ምርትና አገልግሎት ማሻሻሉን ገልጿል ።

የቴሌብር አገልግሎት ከ27.2 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን ማፍራት የቻለ ሲሆን ባለፉት ስድስት ወራት በአጠቃላይ በኢኮኖሚው ውስጥ የ168.1 ቢሊዮን ብር የግብይት መጠን በማንቀሳቀስ በቴሌ ብር 82.5 ሚሊዮን ብር ገቢ ማስገኘት ተችሏል።

Read 375 times

About Us

Shop In Addis is an online web-based classifieds platform that offers buyers and sellers a unique opportunity to effectively reach their target audience.

Disclaimer

All items listed here and the information related to it is provided and maintained by the seller. Shop in Addis is not responsible and can not guarantee the accuracy or completeness of these lists. 

  • Meet the seller in person and inspect items before paying.
  • Report the listing if you have any doubt.

News Letter

Subscribe our Email News Letter to get Instant Update.